ሻምፒዮኑ ኢትዮጵያ መድን ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ሻምፒዮኑ ኢትዮጵያ መድን ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 7/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት ሁለተኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ሀድያ ሆሳዕናን 3 ለ 2 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ወገኔ ገዛኸኝ፣ አቡበከር ሳኒ እና ረመዳን የሱፍ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ተመስገን ብርሃኑ እና ጫላ ተሺታ ለሀድያ ሆሳዕና ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን ነጥቡን ወደ 70 ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱም 21ኛ ድሉን አሳክቷል።
በአንጻሩ በሊጉ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሀድያ ሆሳዕና በ47 ነጥብ 5ኛ ደረጃን ይዟል።
ቀን ላይ በተደረገ የ35ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 0 አሸንፏል።