የደርቢው ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል 

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 7/2017(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ተጠባቂ ጨዋታ ናይጄሪያዊው ዲቫይን ዋቹኩዋ በ28ኛው እና አማኑኤል አድማሱ በ66ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን ወደ 59 ከፍ አድርጓል። በሊጉም 17ኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ45 ነጥብ 7ኛ ደረጃን ይዟል።

የሁለቱ ክለቦች 50ኛ የሊጉ የደርቢ ጨዋታ 
በኢትዮጵያ ቡና የበላይነት ተጠናቋል። 

ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሻምፒዮኑ ኢትዮጵያ መድን ከሀድያ ሆሳዕና ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም