በጊንጪ ከተማ አቅራቢያ የተገነባው ኬኛ ቢቨሬጅ ፋብሪካ ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
በጊንጪ ከተማ አቅራቢያ የተገነባው ኬኛ ቢቨሬጅ ፋብሪካ ተመረቀ

ጊንጪ ፤ሰኔ 7/2017 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን ጊንጪ ከተማ አቅራቢያ የተገነባው ኬኛ ቢቨሬጅ ፋብሪካ ተመርቆ አገልግሎት ጀመረ።
በፋብሪካው ምረቃ ላይም የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሸመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ፋብሪካው በክልሉ ምእራብ ሸዋ ዞን በ110 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን 22 ቢሊዮን ብር መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ የተደረገበት መሆኑም ታውቋል።
ፋብሪካው ከ4 ሺህ በላይ ባለ አክሲዮኖች የተቋቋመና ከ250 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በቀጥታ የስራ እድል የፈጠረ መሆኑም ተመላክቷል።
እንዲሁም በምርት አቅርቦትና በሌሎች የእሴት ሰንሰለት ለ1 ሺህ ዜጎች በተዘዋዋሪ የስራ እድል ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ታውቋል።