በሲዳማ ክልል ለግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች እውቅናና ሽልማት እየተሰጠ ነው

ሀዋሳ፤ሰኔ 6/2017 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል ለግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች የተዘጋጀ የእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ያዘጋጀው መርሃ ግብር"ታማኝ ግብር ከፋይ ብርቱ የልማት አርበኛ ነው" በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ዛሬ እውቅናና ሽልማት የሚሰጣቸው ግብር ከፋዮች የሁለት የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ጨምሮ በቁጥር 55 ሲሆኑ ከ2 እስከ 57 ሚሊየን ብር በላይ ግብር በታማኝነት የከፈሉ መሆናቸው ታውቋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፤ ባለሃብቶችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም