ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሀቢብ ከማል በ45ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ጎል ድሬዳዋ ከተማን መሪ አድርጎ ነበር።

ከእረፍት መልስ ሀብታሙ ታደሰ በ54ኛው ደቂቃ  የሲዳማ ቡናን የአቻነት ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በ47 ነጥብ 6ኛ  ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ድሬዳዋ ከተማ በ40 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። ቡዱኑ ከወራጅ ቀጠና ለመራቅ የሚያስችለውን ሶስት ነጥብ የማግኘት እድል አልተጠቀመበትም።

በ34ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ወላይታ ድቻ ከባህር ዳር ከተማ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም