ምክር ቤቱ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ እና የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2017(ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ እና የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ።




ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ምክትል ሰብሳቢ እና የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ሹመት በሁለት ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።




በዚህም አቶ ተስፋዬ ንዋይን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ እንዲሁም አቶ ተክሊት ይመስል እና ወይዘሮ ነሲም አሊን የሥራ አመራር ቦርድ አባላት አድርጎ ሹሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም