የ35ኛ ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር ላይ ማሻሻያ ተደረገ 

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ። 

ማሻሻያው የክለቦችን ውጤት እና የመጫወቻ ሜዳዎች ያሉበትን ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን ገልጿል። 

በዚህም መሰረት እሁድ ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ይደረጉ የነበሩ የሊጉ ጨዋታዎች ወደ ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም የተሳቡ ሲሆን እሁድ ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ ነጥባቸው ከ39 በታች የሆኑ ሶስት ክለቦች ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት በተለያዩ ሜዳዎች ይደረጋሉ።

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ለምርቃት ዝግጅት የሚፈለግ በመሆኑ የሊጉ 35ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎችም ሰኞ እና ማክሰኞም በወንጂ ሁለገብ ስታዲየም እንደሚቀጥሉ ማህበሩ ገልጿል።

የ34ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎችን ውጤት መሰረት በማድረግ ተጨማሪ አራተኛ ሜዳ ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችልም አመልክቷል። 

ውጤቶችን መሰረት በማድረግ የ35ኛ እና የ36ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ለውጥ ሊደረግ እንደሚችል የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቆ ነበር።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም