የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ በባህር ዳር መካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ በባህር ዳር መካሄድ ጀመረ

ባህር ዳር፤ ሰኔ 4/2017 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት 3ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ መካሄድ ጀመረ።
የአማራ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሰላም ጉባኤ "ኃይማኖቶች ለሰላም፣ ለመከባበርና ለአብሮነት" በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በጉባኤው ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ፣ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሓፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የኃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ ከተለያዩ ክልሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች ታድመዋል።
በዚሁ ሀገር አቀፍ ጉባኤ ላይ ከ400 በላይ ተሳታፊዎች የሚታደሙ ሲሆን ሁለት ሰነዶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።