የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን ድል ቀንቶታል 

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2017(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድን መቻልን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ወገኔ ገዛኸኝ በ42ኛው እና ዩጋንዳዊው አለን ካይዋ በ68ኛው ደቂቃ ላይ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ውጤቱን ተከትሎ የሊጉን ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንሳቱን ያረጋገጠው ኢትዮጵያ መድን ነጥቡን ወደ 67 ከፍ አድርጓል።  በውድድር ዓመቱ 20ኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በሊጉ 8ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቻል በ44 ነጥብ 9ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች አላሸነፈም።                                 

ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል ከነማ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም