ሀድያ ሆሳዕና ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ሀድያ ሆሳዕና ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 2/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 34ኛ ሳምንት ሀድያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ ጨዋታ ፀጋአብ ግዛው በ93ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሏን አስቆጥሯል።
ሀድያ ሆሳዕና በ47 ነጥብ ደረጃውን ከ9ኛ ወደ 5ኛ ከፍ ሲያደርግ የአምናው የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ40 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።
ቀን ላይ በተደረጉ ሌሎች የ34ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሃዋሳ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ፣ መቀሌ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ ቡና አንድ አቻ ተለያይተዋል።