ሃዋሳ ከተማ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ሃዋሳ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 2/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሃዋሳ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአማካይ ተጫዋቹ ቢንያም በላይ በ87ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቧን አስቆጥሯል።
ድሉን ተከትሎ ሃዋሳ ከተማ በ47 ነጥብ ደረጃውን ከ7ኛ ወደ 4ኛ ከፍ አድርጓል።
ከሊጉ የወረደው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ19 ነጥብ የመጨረሻውን 18ኛ ደረጃን ይዟል።
ምሽት 12 ሰዓት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሀድያ ሆሳዕና ይጫወታሉ።