በሊጉ የተገናኙት አርባምንጭ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በሊጉ የተገናኙት አርባምንጭ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 34ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሃ ግብር አርባምንጭ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ቀን 9 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ግብ ሳያስተናግድ ተጠናቋል።
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ስሑል ሽረ እና አዳማ ከተማ ይጫወታሉ።