ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2017(ኢዜአ)፦ ሲዳማ ቡና የ2017 የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።
ሲዳማ ቡና ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረገውን የ2017 ኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።
ለሲዳማ ቡና የማሸነፊያ ግቦቹን መስፍን ታፈሰ እና ሀብታሙ ታደሰ ሲያስቆጥሩ ወላይታ ድቻን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ ካርሎስ ዳምጠው አስቆጥሯል።
ወላይታ ድቻ ባለፉት ተከታታይ ሁለት አመታት የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታዎችን መሸነፋቸው ይታወሳል።
ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በሚቀጥለው አመት ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ይሳተፋል።