የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በጂንካ ከተማ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በጂንካ ከተማ እየተከበረ ነው
ጂንካ፤ግንቦት 29/2017(ኢዜአ)፦1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በጂንካ ከተማ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነስርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።
በቀድሞው የጂንካ አየር ማረፊያ በአሁኑ አንድነት የመዝናኛ ፓርክ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በዓሉ በድምቀት እየተከበረ ነው።
በክብረ በዓሉ የኢድ- ሰላት እና ተክቢራን ጨምሮ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ተከናውነዋል።
የአሪ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ጀማል ሙሐመድ እና የጂንካ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ኡመርዲን ግርማን ጨምሮ የእምነቱ አባቶች በተገኙበት ነው በዓሉ እየተከበረ ያለው።
የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ፣የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሲሳይ ጋልሺ እና ሌሎች የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችም በክብረ በዓሉ ላይ ታድመዋል።