የስሎቪኒያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ - ኢዜአ አማርኛ
የስሎቪኒያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 28/2017(ኢዜአ)፦ የስሎቪኒያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ናታሳ ፒርክ ሙሳር(ዶ/ር) በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለፕሬዚዳንቷ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የስሎቪኒያ ፕሬዚዳንት ማዳም ናታሳ ፓርክ ሙሳር(ዶ/ር) ለይፋዊ ጉብኝት ትናንት ምሽት ነው አዲስ አበባ የገቡት።
ፕሬዚዳንቷ በዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ ሀውልት ስር የአበባ ጉንጉን ዛሬ አስቀምጠዋል፤ መታሰቢያውንም ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ እና የስሎቪኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ማርኮ ሹትሲን በተገኙበት 3ኛው የፖለቲካ ምክክር መድረክ ትናትን መካሄዱ ይታወሳል።
የፖለቲካ ምክክሩ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማሳደግ፣ አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለመለየት እና በሀገሮቹ መካከል ንግድና ኢንቨስትመንትን ማሳደግ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን ለመንደፍ ጥሩ አጋጣሚ እንደሚፈጥር ነው የተገለጸው።
ኢትዮጵያ እና ስሎቪኒያ ትብብርን በማጠናከር ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በጋራ የመስራት ፍላጎት አላቸው።
ኢትዮጵያ በቀጣናው ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃም ጠቃሚ አጋር መሆኗ ተነስቷል።
ፕሬዚዳንቷ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት በተለያዩ ዘርፎች ማለትም ኢንቨስትመንትንና ንግድን ጨምሮ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር እንደሚያስችልም ተገልጿል።