ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ልዩ ቆይታ በክፍል አንድ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ልዩ ቆይታ በክፍል አንድ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

ኢትዮጵያዊነት የጋራ እጣ ፈንታ እና ከግል መሻት የተሻገረ ማንነት ነው፤
እንደ ህዝብ የምንደርስበትን ግብና መሻት ልናሳካ የምንችለው በዚህ ትልቅ ማንነት ስር ነው፤
ኢትዮጵያዊነት ከትናንት እስከ ዛሬ፣ ከዛሬ እስከ ነገ ማዕቀፍ እንጂ ሲመችና ሳይመች የሚለዋወጥ ማንነት አይደለም፤
ኢትዮጵያዊነት የማይቆም፣ የነበረ፣ ያለና የሚኖር እንደጅረት የሚፈስ ማንነት ነው፤
ኢትዮጵያዊነት የብሄራዊ ጥቅም አካል ነው፤
ብሔራዊ ጥቅምን ማሳካት እና ማበልጸግ የሚቻለው ብሄራዊ ትርክት መገንባትና ትውልድ መስራት ሲቻል ነው፤
የኢትዮጵያዊነት ማንነት ለሌሎች ማንነት ሁሉ ስር ነው፤ ሁሉም ማንነቶች በኢትዮጵያዊነት ማንነት ስር የሚወድቁ ናቸው
ሀገር የቅብብሎሽ ውጤት በመሆኑ ትልውድ እያሰቡ መስራትን ይጠይቃል፤
ሀገር ለመገንባት ትናንትን ከዛሬ፤ ዛሬን ከነገ በማስተሳሰር እየሰራን ነው፤
ትናንትን በመጠገን ብቻ ነገ አይሰራም፤ የዛሬ ክፍተትን በመፍታት የተሻለ ነገ ለመገንባት እየተሰራ ነው፤
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና አንድነት ከማንኛውም ኃይል መጠበቅ የሚያስችሉ የጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት ተገንብተዋል፤
ፈተና እና ስጋት በሰው ውስጥ ያለን እምቅ አቅም ተጠቅሞ ውጤት ማምጣት የሚያስችሉ ጉዳዮች ናቸው፤
ሉዓላዊነታችንን በተማሏ ሁኔታ ከማንም ኃይል መጠበቅ እንችላለን፤
መንግስት ከፈተናዎች ውስጥ እድልን ፈልቅቆ በማውጣትና በመጠቀም ያከናወናቸው ስራዎች ኢትዮጵያን ተጠቃሚ አድርገዋታል፤
ለውጡ በዓለም ላይ ከፍተኛ ድጋፍና ውዳሴ ካስተናገዱ ለውጦች መካከል አንዱ ነው፤
መዳረሻችን ብልጽግና፣ የጸናችና ከልመና የተላቀቀች ኢትዮጵያን ማየት ነው፤
ውዳሴም እርግማንም ቢመጣ ብዙ ሚዛን የሚያስጥል አልሆነም ሚዛንን ማስጠበቅ የተቻለው መርሃችን መልህቃችን ስለሆነ ነው፤
የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና የዴሞክራሲ ባህልን ለማጎልበት የተወሰዱ እርምጃዎች በአብላጫው ውጤት አስገኝተዋል፤
የለውጡ መንግስት የተረከባት ኢትዮጵያ በእዳ የተዘፈቀች፣ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ስራ ያቆሙባት፣ የተቋማት ድቀት፣ አሳሪ ሕጎች እና ከፋፋይ ትርክት የነገሰባት ነበረች፤
መዋቅራዊ ችግሮችን ለመፍታት የተወሰዱ እርምጃዎች በአሁኑ ሰዓት የተሻለ ቁመና ያላት ኢትዮጵያ እንድትኖር አስተዋጽኦ አድርጓል፤