ፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ከብክለት የፀዳች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታን ፈጥሯል - ኢዜአ አማርኛ
ፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ከብክለት የፀዳች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታን ፈጥሯል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2017(ኢዜአ)፦ የመጀመሪያው ዙር ፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ከብክለት የፀዳች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ መፍጠሩን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ ገለጹ።
ሁለተኛው ዙር ፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ከግንቦት 28/2017 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ንቅናቄውን አስመልክቶ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ የመጀመሪያው ዙር ፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ውጤታማ በሆነ መልኩ ተካሂዷል።
የመጀመሪያው ዙር ፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ከብክለት የፀዳች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታን መፍጠሩን አንስተዋል።
ሁለተኛው ዙር ፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ከግንቦት 28/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለስድስት ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚካሄድ ገልጸው፤ በአንደኛው ዙር የተጀመሩ ተግባራትን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ያግዛል ብለዋል።
በንቅናቄው የውሀ ብክለትን መከላከል፣ የፅዳት ዘመቻና የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስራዎች ወጥ በሆነ መልኩ እንደሚተገበርም አስታውቀዋል።