የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሻርጃ ከተማ በረራ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሻርጃ ከተማ በረራ ጀመረ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሻርጃ ከተማ ዛሬ ማምሻውን የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት ጀምሯል።
በሣምንት አራት ጊዜ የሚደረገው ይህ የበረራ አገልግሎት፤ መንገደኞች ወደ ሻርጃ ከተማ በተቀላጠፈ አማራጭ በቀላሉ እንዲጓዙ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመካከለኛው ምሥራቅ ከ17 በላይ መዳረሻዎች እንዳሉት እና ከ100 በላይ ሳምንታዊ የመንገደኞችና የካርጎ አገልግሎት በረራዎችን እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ወደ ሻርጃ ከተማ የተጀመረው የበረራ አገልግሎት በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን የንግድ፣ ቱሪዝምና የባህል ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚያስችልም ተጠቅሷል፡፡