ቀጥታ፡

ሃዋሳ ከተማ ድል ቀንቶታል 

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 23/2017 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ32ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሃዋሳ ከተማ መቻልን 3 ለ 1 አሸንፏል። 

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዓሊ ሱሌይማን፣ ተባረክ ሄፋሞ እና አቤነዘር ዮሐንስ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ምንይሉ ወንድሙ በፍጹም ቅጣት ምት ለመቻል ብቸኛዋን ጎል አስቆጥሯል። 

የመቻል ተከላካይ አስቻለው ታመነ በ39ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። 

ሃዋሳ ከተማ ድሉን ተከትሎ በ41 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 9ኛ አሻሽሏል። በሊጉም 10 ድሉን አስመዝግቧል። 

በአንጻሩ በሊጉ 7ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቻል በ43 ነጥብ 5ኛ ደረጃን ይዟል። 

የሃዋሳ ከተማው አጥቂ ዓሊ ሱሌይማን በሊጉ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 15 በማድረስ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት መሪነቱን አጠናክሯል። 

በ32ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ ከፋሲል ከነማ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም