በመዲናዋ የተከናወኑ እና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች መንፈስን የሚያድሱ እና ርዕይን የሚሰንቁ ናቸው -ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት - ኢዜአ አማርኛ
በመዲናዋ የተከናወኑ እና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች መንፈስን የሚያድሱ እና ርዕይን የሚሰንቁ ናቸው -ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት
አዲስ አበባ፤ግንቦት 22/2017(ኢዜአ)፦በመዲናዋ የተከናወኑ እና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች መንፈስን የሚያድሱ እና ርዕይን የሚሰንቁ ናቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ኢርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጉብኝቱ በኋላ ብፁዓን አባቶችን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው በተለያዩ ከተማ አቀፍ ጉዳዮች እና የጋራ ስራዎች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ከንቲባዋ የሀገራችን እና የአህጉራችን መዲና እና የዓለም አቀፉ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ መናገሻ የሆነች አዲስ አበባን ይበልጥ ለመለወጥ በትጋት እየሰራን ነው ብለዋል።
ብፁዓን አባቶቻችን በምክር እና ጸሎት ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ስላሉ እና ስለሚያበረታቱን ከልብ እናመሰግናለን ነው ያሉት ከንቲባዋ።
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በበኩላቸው፥ ከለውጡ ጀምሮ መንግስት በከተማዋ ላከናወናቸው የልማት ስራዎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
በመዲናዋ የተከናወኑ እና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች መንፈስን የሚያድሱ እና ርዕይን የሚሰንቁ ናቸው ብለዋል።
በቀጣይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ይበልጥ ተቀራርባ እንደምትሰራ እና እነርሱም የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።