የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁ ታላቅ ስኬት ነው-የሰላም ሚኒስቴር - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁ ታላቅ ስኬት ነው-የሰላም ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፤ግንቦት 20/2017(ኢዜአ)፦የሰላም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅደስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ጉባኤውን በሰላም በማጠናቀቁ ለብፁዓን አባቶችና ለዕምነቱ ተከታዮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ለሀገረ መንግስት ግንባታ፣ኢትዮጵያዊ አብሮነት እንዲሁም በሀገር ሰላም ግንባታ ሂደቶች እንደሌሎች የሀገራችን ሃይማኖቶች ሁሉ ጉልህ ሚና ስትጫወት መቆየቷን ነው የገለጸው።
ሚኒስቴሩ፥አሁንም ይህንን ተግባሯን እያከናወነች እንዳለ እንደሚገነዘብ ገልጾ፤ ለዚህም ልዩ አክብሮቱን ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ከቤተክርስትያኒቷ ጋር የወል ግባችን የሆኑት የሰላም እና የሀገር ግንባታ ሥራዎች ዙሪያ ተቀራርቦ ለመስራት ከምንግዜውም በበለጠ ያለውን ቁርጠኝነት ጠቁሟል።
በጉባኤው ተመርጠው ኃላፊነትን ከተረከቡት አባቶች ጋርም ተቀራቦ የመስራት ዝግጁነት ገልጾ፥ ቤተ ክርስቲያኒቷ በሰላም፣በማኅበራዊ ልማት እና በሀገር ግንባታ የሚጠበቅባትን ሀገራዊ ኃላፊነት እንድምትወጣ ያለውን ተስፋ መግለጹን ኢዜአ ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።