ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል።

ኢንስቲትዩቱ ከምድር እስከ ህዋ ድረስ የሚገኙ መረጃዎችን በመተንተን የምርምር ስራዎችን የሚያከናውን ተቋም መሆኑም ተገልጿል።


 

የምርምር ስራዎቹ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እየተተነተኑ ቅድመ ትንበያና የትንበያ ስራዎችን በመስራት ለሚመለከታቸው ተቋማት እንዲጠቀሙበት እንደሚያስችል ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የጂኦስፓሻል ጥናትና ምርምር በተለያዩ ዘርፎች የተዋቀረ ሲሆን ዛሬ በየሥራ ክፍሎቹ የሚከናወኑ የመረጃ ትንተና እና ምርምር ስራዎች ምልከታ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም