ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20/2017 (ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተወያይተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ዛሬ ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሀገር ግንባታ ተገቢውን አስተዋጽኦ እንድታበረክት መንግሥት የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚወጣም ገልጸዋል።

አዲስ ለተመደቡት ብጹአን አባቶች መልካም የሥራ ዘመን ተመኝቻለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም