የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በነሐሴ ወር ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በነሐሴ ወር ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2017 (ኢዜአ)፦የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ነሐሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ሊጉ በነሐሴ እንዲጀመር የተወሰነው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሚያደርገው ዝግጅት እና ጨዋታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን ገልጿል።
የውድድሩ ቦታ እና ሌሎች መረጃዎች በቀጣይ እንደሚገለጽ ፌዴሬሽኑ በመረጃው አመልክቷል።