ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ጋር መወያየታቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒን በሮም ፓላዞ ቺጊ አግኝቼ ውይይት አካሂደናል ሲሉ ገልጸዋል።


 

ውይይታችን በኢትዮጵያ እና ጣሊያን መካከል የሁለትዮሽ ትስስራችንን በማጠናከር ለአዲስ ኢንቨስትመንት እና የኢኮኖሚ ትብብር እድሎችን መፍጠር ላይ ያተኮረ ነበር ብለዋል።

የረጅም ዘመን ወዳጅነት ላይ በተመሠረተው የሁለቱ ሀገሮቻችንን ትብብር በተለያዩ መስኮች ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ፅኑ አቋማችንንም እንደገና አረጋግጠናል ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም