ቀጥታ፡

13ኛው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች እና 4ኛው ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና መካሄድ ጀምሯል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2017(ኢዜአ)፦ 13ኛው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች እና 4ኛው ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተለያዩ የማጣሪያ እና ፍፃሜ ውድድሮች ተከናውነዋል።

በሻምፒዮናው የመጀመሪያ ቀን የፍፃሜ ውድድሮች ተካሂደዋል።

በዚህም በ3000 ሜትር መሰናክል ሴቶች አለምናት ዋለ ከአማራ ፖሊስ አንደኛ ኬና ቱፋ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ እንዲሁም ዘረቱ ዳባ ከሸገር ሲቲ በሶስተኝነት አጠናቀዋል።


 

በ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶችም እንዲሁ ዲንቃ ፍቃዱ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አንደኛ ሀይሉ አያሌው ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሁለተኛ እንዲሁም ጀማል ጁሀር ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ሶስተኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል።

በጦር ውርወራ ሴቶች በተከናወነ ውድድር ሩት አሬሮ ከአዳማ ከተማ አንደኛ ዱኩ ኔንቆ ከሸገር ሲቲ ሁለተኛ

እንዲሁም የሺወርቅ አንማው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስተኛ በመሆን ማጠናቀቃቸውን ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።


 

በከፍታ ዝላይ ወንዶች  በተከናወነ ውድድር ዳል ማች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኦስሎ ኡጁሉ ከመቻል እንዲሁም ፓሊፓ ኡማን ከሲዳማ ቡና እንደየቅደም ተከተላቸው ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፈዋል።

ሻምፒዮናው ከሰዓት በኋላም በተለያዩ ውድድሮች እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም