አዳማ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2ለ0 አሸንፈ - ኢዜአ አማርኛ
አዳማ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2ለ0 አሸንፈ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 31ኛ ሳምንት አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ነቢል ኑሪ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ አዳማ ከተማ በ29 ነጥብ ደረጃውን 16ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ከመውረድ ስጋት ለመትረፍ በሚደረገው ፋክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። በሊጉ 7ኛ ድሉንም አሳክቷል።
በአንጻሩ በሊጉ 8ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የአምናው የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ39 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በአሁኑ ሰዓት ወላይታ ድቻ ከመቻል ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።