ክሮሺያ በተካሄደ ኮንቲኔንታል ቱር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ - ኢዜአ አማርኛ
ክሮሺያ በተካሄደ ኮንቲኔንታል ቱር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2017(ኢዜአ)፦ በክሮሺያ ዛግሬብ በተካሄደው ኮንቲኔንታል ቱር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
በሴቶች 1ሺህ 500 ሜትር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች።
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 3ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ14 ማይክሮ ሴኮንድ እንደወሰደባት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
አትሌት ብርቄ ኃየሎም በበኩሏ በ3ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ ከ19 ማይክሮ ሴኮንድ ውድድሩን በሁለተኝነት ስታጠናቅቅ አትሌት ሳምራዊት ሙልጌታ ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሳለች።
በወንዶች 5ሺህ ሜትር አትሌት ቢኒያም መሀሪ በ13 ደቂቃ ከ03 ሴኮንድ ከ57 ማይክሮ ሴኮንድ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቁንም የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል።