በአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ የልዑካን ቡድን በትናንትናው እለት ወደ ደቡብ ሱዳን አቅንቷል - ኢዜአ አማርኛ
በአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ የልዑካን ቡድን በትናንትናው እለት ወደ ደቡብ ሱዳን አቅንቷል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2017(ኢዜአ)፦ በአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫኪርና ምክትል ፕሬዚደንቱ ቤንጃሚን ቦልሜል ጋር ተወያይተዋል።
የልዑካን ቡድኑ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተላከ መልዕክት ባደረሰበት ወቅት የደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ጋር የተሳሰረ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንትና ምክትላቸውም ኢትዮጵያ ከቀድሞ ጀምሮ እስከ አሁን የዘለቀና የማይናወጥ ድጋፍ እያደረገች መቆየቷን በማውሳት ምስጋናና አድናቆታቸውን መግለፃቸውንና ይሄው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን የደረሰን ዜና ያስረዳል።
የልዑካን ቡድኑ ትናንት ማምሻውን ውይይቱን አጠናቆ ተመልሷል።