ቶተንሃም ሆትስፐርስ የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
ቶተንሃም ሆትስፐርስ የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2017 (ኢዜአ)፡- በዩሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ማንችስተር ዩናይትድን 1 ለ 0 በማሸነፍ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል።
ማምሻውን በሳን ማሜስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሬናን ጆንሰን በ42ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ቶተንሃም ሆትስፐርስ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ አንስቷል። በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በቀጣዩ የውድድር ዓመት መሳተፉንም አረጋግጧል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ከ41 ዓመት በአውሮፓ መድረክ ዋንጫ ማንሳት ችሏል። ቡድኑ ከ17 ዓመታት በኋላ ከዋንጫ ጋር ታርቋል።
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያሳለፈውን መጥፎ የውድድር ዓመት በዋንጫ ቋጭቷል።
ዩናይትድ በዩሮፓ ሊግ የውድድር ጉዞው የመጀመሪያ ሽንፈቱን በፍጻሜው ጨዋታ አስተናግዷል።
ማንችስተር ዩናይትድ በመጥፎው የውድድር ዓመት ቆይታው ዋንጫ እና የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ የሚያገኝበትን ብቸኛ እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።