ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።

14ኛው የኢትዮ-ሩሲያ የበይነ መንግስታት የወታደራዊ እና ቴክኒካዊ ትብብር የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ በሩሲያ ሞስኮ መካሄድ ጀምሯል።

በስብሰባው በመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ የተመራ ልዑክ እየተሳተፈ ይገኛል።

ሚኒስቴር ዴኤታዋ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ እና ሩሲያ ወታደራዊ እና ቴክኒካዊ ትብብር የሀገራቱ ለረጅም ጊዜ የቆየ ትስስር እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ቁልፍ ምሰሶ እንደሆነ ገልጸዋል።


 

የጋራ ኮሚቴው የኢትዮጵያ እና ሩሲያን ወታደራዊ ትብብር ለመገምገም እና በአቅም ግንባታ ኢኒሼቲቮች የኢትዮጵያን የመከላከያ አቅም ማጠናከር የሚያስችል ማዕቀፍ መሆኑን አመልክተዋል።

በቴክኖሎጂ ሽግግር ያሉ እድሎችን መጠቀም እንደሚያስችልም ጨምረው ተናግረዋል።

የጋራ ኮሚቴው የሩሲያ ሰብሳቢ አናቶሊ ፑንቹክ ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ወታደራዊ እና የቴክኒክ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም