የማንችስተር ሲቲ እና ቦርንማውዝ ተጠባቂ መርሃ ግብር - ኢዜአ አማርኛ
የማንችስተር ሲቲ እና ቦርንማውዝ ተጠባቂ መርሃ ግብር

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከቦርንማውዝ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኢትሃድ ስታዲየም ይደረጋል።
ማንችስተር ሲቲ በ65 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቦርንማውዝ በ53 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ከቀሪ ሁለት ጨዋታዎቹ አራት ነጥብ የሚፈልገው ማንችስተር ሲቲ የዛሬውን መርሃ ግብር ማሸነፍ በጣም ወሳኝ ነው።
ለቦርንማውዝ ማሸነፍ ደረጃውን ከማሻሻል የዘለለ ትርጉም የለውም።
በማንችስተር ሲቲ 10 ዓመታት ያገለገለው የ33 ዓመቱ ቤልጂየማዊ ኮከብ ኬቨን ደ ብሮይን በኢትሃድ የመጨረሻ ጨዋታውን ያደርጋል። ለተጫዋቹ የሽኝት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶለታል።
በሌላኛው የ37ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሃ ግብር ክሪስታል ፓላስ ከዎልቭስ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የኤፍኤ ካፕ ዋንጫ አሸናፊው ክሪስታል ፓላስ በ49 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል። ዎልቭስ በ41 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ሁለቱ ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ እና ማንችስተር ሲቲ በነበራቸው የኤፍኤ ካፕ የዋንጫ ጨዋታ ምክንያት በተስተካካይ መርሃ ግብር የተያዙ ናቸው።