ብራይተን የሊጉን ሻምፒዮን ሊቨርፑልን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 11/2017 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ብራይተን ኤንድ ሆብ አልቪዮን ሊቨርፑልን 3 ለ 2 አሸንፏል።

ማምሻውን በአሜክስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ያሲን አያሪ፣ ካሩ ሚቶማ እና ጃክ ሂንሺልውድ ለብራይተን ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሀርቪ ኤሊዮት እና ዶምኒክ ስቦዝላይ ለሊቨርፑል ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ብራይተን በ58 ነጥብ ደረጃውን ከ9ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል።

በሊጉ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የሊጉ የዋንጫ ባለቤት ሊቨርፑል 83 ነጥብ ላይ ረግቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም