ባህር ዳር ከተማ እና መቻል ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ባህር ዳር ከተማ እና መቻል ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 11/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት
ባህር ዳር ከተማ እና መቻል ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተደርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ ባህር ዳር ከተማ በ48 ነጥብ 3ኛ፣ መቻል በ42 ነጥብ 5ኛ ደረጃን ይዘዋል።
በ30ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከስሑል ሽሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።