ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የልማት ዕቅዶች ለሁሉን አቀፍ የሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት የሰጡ ናቸው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የልማት ዕቅዶች ለሁሉን አቀፍ የሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት የሰጡ መሆናቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡ 

20ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት (ILO) የሌበር ቤዝድ ፕራክቲሽነርስ አህጉራዊ ኮንፈረንስ በአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በመክፈቻው መርኃ ግብር እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የልማት ዕቅዶች ለሁሉን አቀፍ ሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት የሰጡ ናቸው። 

ይህም በመላ አገሪቷ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ማስቻሉን አብራርተዋል፡፡ 

ስብሰባው በዘርፉ ባሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ በመምከር የተሻለ መንገድ ለመቅረጽ እንዲሁም በሚሊዮን የሚቆጠሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚመክር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ስብሰባው "የማይበገር ማህበረሰብ እና ጤናማ አካባቢ የሰው ኃይልን በብዛት የሚጠቀሙ የኢንቨስትመንት ፕሮግራም አካሄዶች" በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።

ከዛሬ ግንቦት 11 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄደውን ጉባኤ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከዓለም የሥራ ድርጅት (ILO) ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጁት ነው ።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም