የፕሪሚየር ሊጉ 30ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል - ኢዜአ አማርኛ
የፕሪሚየር ሊጉ 30ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 11/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ባህር ዳር ከተማ ከመቻል ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።
በሊጉ ባህር ዳር ከተማ በ47 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ መቻል በ41 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በጥሩ ወቅታዊ ብቃት ላይ የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች በጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በ30ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከስሑል ሽሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ሀድያ ሆሳዕና በ41 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በአንጻሩ ተጋጣሚው ስሑል ሽሬ በ21 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
የዛሬ ጨዋታዎች በዋንጫ ፉክክሩ እና ላለመውረድ በሚደረገው ትግል ላይ ተጽእኖ ይኖራቸዋል።