ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 10/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጌታነህ ከበደ ለፋሲል ከነማ፣ አዲስ ግደይ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ዩጋንዳዊው የፋሲል ከነማ ተጫዋች ማርቲን ኪዛ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ በ36 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ሲይዝ የአምናው የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ39 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዛሬ በተደረጉ ሌሎች የ30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን 2 ለ 0 ሲረታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያለ ምንም አቻ ተለያይተዋል።