አትሌት መዲና ኢሳ በማንቼስተር በተካሄደ የ10 ኪ.ሜ ሩጫ አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
አትሌት መዲና ኢሳ በማንቼስተር በተካሄደ የ10 ኪ.ሜ ሩጫ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ግንቦት 10/2017 ( ኢዜአ) :-አትሌት መዲና ኢሳ በማንቼስተር በተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር የሴቶች ውድድር አሸንፋለች።
አትሌት መዲና ውድድሩን በ30 ደቂቃ ከ42 ሰኮንድ በመግባት በአንደኝነት አጠናቃለች።
በውድድሩ የተሳተፈችው ሌላኛዋ አትሌት ጎይተቶም ገ/ስላሴ በ31 ደቂቃ 11 ሰኮንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቋን የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።