ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥብ ተጋርተዋል 

አዲስ አበባ ፤ግንቦት 10/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው ዛሬ ረፋድ ላይ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል።

ውጤቱን ተከትሎ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ14 ነጥብ የመጨረሻውን 18ኛ ደረጃ ይዟል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ33 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በ30ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት፣ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸው ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም