የአርሰናል እና ኒውካስትል ዩናይትድ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ - ኢዜአ አማርኛ
የአርሰናል እና ኒውካስትል ዩናይትድ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2017(ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት አርሰናል ከኒውካስትል ዩናይትድ ጋር ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል።
አርሰናል በ68 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ኒውካስትል ዩናይትድ በ66 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
መድፈኞቹ በዛሬው ጨዋታ ቢያንስ አንድ ነጥብ ካገኙ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መሳተፋቸውን ያረጋግጣሉ።
በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመሳተፍ አራት ነጥብ የሚያስፈልገው ኒውካስትል ዩናይትድ የዛሬው ጨዋታ ለአውሮፓ መድረክ ተሳትፎ ህልሙ ወሳኝ የሚባል ነው።
ሌላኛው የሻምፒዮንስ ሊግ ቦታን ለማግኘት እየተፎካከረ የሚገኘው ኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ለንደን ስታዲየም በማቅናት ከቀኑ 10 ሰዓት ከ15 ላይ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ይጫወታል።
ኖቲንግሃም ፎረስት በ62 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ኤቨርተን ከሳውዝሃምፕተን ከቀኑ 8 ሰዓት፣ ብሬንትፎርድ ከፉልሃም እና ሌይስተር ሲቲ ከኢፕስዊች ታውን በተመሳሳይ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።