ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ 

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 10/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

የመጀመሪያው ጨዋታ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከ30 በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ መካከል በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይከናወናል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ13 ነጥብ የመጨረሻውን 18ኛ ደረጃ ይዟል። ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ32 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ ይጫወታሉ። 

ኢትዮጵያ ቡና በ48 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ቡናማዎቹ ካሸነፉ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ዘጠኝ ዝቅ ያደርጋሉ።  
        
ተጋጣሚው አዳማ ከተማ በ26 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ጨዋታው ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት እያደረገ ላለው ትግል ወሳኝ የሚባል ነው።

የዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ያገናኛል።

ፋሲል ከነማ በ35 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ38 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም