ኢትዮጵያ የድሮን ትርኢት አካሄደች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የድሮን ትርኢት አካሄደች

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ 1 ሺህ 500 ድሮኖች የተሳተፉበት የድሮን የአየር ላይ ትርኢት አካሄደች።
በትሪኢቱ የተሳተፉ የድሮኖች ቁጥር በአፍሪካ የመጀመሪያ እንደሚያደርገውም ተገልጿል።
በትርኢቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፤ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፣ ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ እንግዶች ታድመዋል።
የድሮን ትርኢቱ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 አካል ሲሆን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በጋራ የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።
ድሮኖቹም ዲጂታል ኢትዮጵያ፣ አረንጓዴ አሻራ እና የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን የሚገልፁ ትርኢቶችን አሳይተዋል።