ቀጥታ፡

በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ የተገነባ 23 ኪሎ ሜትር የገጠር መንገድ ተመርቆ ለአገልገሎት ክፍት ሆነ

ወልቂጤ፤ግንቦት 5/2017 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ የተገነባ ከኢናንጋራ _ተርሆኘ_ ጋዛንቸ 23 ኪሎ ሜትር የገጠር መንገድ በክልሉ ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ ር) ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገጠር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ምስጋና ማቴዮስ በወቅቱ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ለመንገዱ ግንባታ ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደርጓል።

መንገዱ በዞኑ እኖር፣ጌታና ቸሃ ወረዳዎችን የሚገኙ ከ20 በላይ ቀበሌዎችን የሚያገናኝ በመሆኑ ለማህበረሰቡ የሚሰጠው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

የመንገዱ ግንባታ በ2012 ዓም ተጀምሮ የዘገየና አሁን ላይ በክልሉ መንግስት በተሰጠው ትኩረት ስራው የተጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል ።

በመንገዱ ምረቃ ስነ ስርአት ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ መሃመድ ኑርዬ ( ዶ/ር)ና የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም