ማንችስተር ዩናይትድ በዌስትሃም ዩናይትድ ተሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ዩናይትድ በዌስትሃም ዩናይትድ ተሸነፈ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ በዌስትሃም ዩናይትድ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸነፈ።
ለዌስትሃም ዩናይትድ የማሸነፊያ ጎሎቹን ሱሴክ እና ጃሮድ ቦውን አስቆጥረዋል።
በሌላ የሊጉ መርሃግብሮች ቶተንሀም ከክሪስታል ፓላስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ሲሸነፉ ኖቲንግሀም ፎረስት ከሌስተር ሲቲ ጋር 2 አቻ ተለያይተዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ዌስትሀም ዩናይትድ በ40 ነጥብ 15ኛ፤ ማንችስተር ዩናይትድ በ39 ነጥብ 16ኛ እንዲሁም ቶተንሀም ሆትስፐርስ በ38 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።