የ28ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ላይ የመጫወቻ ሜዳ እና የመጫወቻ ሰዓት ለውጥ ተደረገባቸው - ኢዜአ አማርኛ
የ28ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ላይ የመጫወቻ ሜዳ እና የመጫወቻ ሰዓት ለውጥ ተደረገባቸው
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 29/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት ቀሪ አራት ጨዋታዎች ላይ የመጫወቻ ሜዳ እና የመጫወቻ ሰዓት ለውጥ ማድረጉን የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።
ጨዋታዎቹን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ለማካሄድ መርሃ ግብር ወጥቶ ነበር።
ይሁንና በሃዋሳ ከተማ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የመጫወቻ ሜዳ እና የሰዓት ለውጥ መደረጉን የውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ አስታውቋል።
በዚሁ መሰረት ቀሪዎቹ የ28ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሎጊታ በሚገኘው በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ይደረጋሉ።
ወላይታ ድቻ ከአርባምንጭ ከተማ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት በሰው ሰራሽ ሜዳው ይጫወታሉ።
ነገ ድሬዳዋ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት፣ ሲዳማ ቡና ከመቻል ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።
የኢትዮጵያ መድን እና ባህር ዳር ከተማ ጨዋታን በተመለከተ ያለውን መረጃ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ አክሲዮን ማህበሩ ገልጿል።