ቀጥታ፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት በትኩረት እየሰራ ነው

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 28/2017(ኢዜአ)፦የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ገለፁ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተቋሙን ለሚቀላቀሉ 300 አዲስ ሠራተኞች በዛሬው ዕለት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሥልጠና መስጠት ጀምሯል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ሥልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት ተቋሙ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ሁለንተናዊ ሪፎርም እያካሄደ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ተቋሙ ቀልጣፋ፣ደህንነቱንና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ዘመናዊ አሰራሮችን እየዘረጋ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባሻገር አገልግሎቱን ለማሳለጥ ብቃት ያለው የሰው ኃይል ማሟላት አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት በሰው ኃይል ልማት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።

በዚህም የነባር ሰራተኞችን አቅም ማጎልበት ጨምሮ ተቋሙን እንደ አዲስ የማደራጀት ስራ መከናወኑን አንስተዋል።

አገልግሎቱ ተቋሙን ለሚቀላቀሉ 300 ሠራተኞች በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሥልጠና መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል።

ሥልጠናው በተቋሙ አጠቃላይ የአሰራር ስርዓትና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም በዲፕሎማቲክ ፕሮቶኮል ላይ ያተኮረ እንደሆነ አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም