ቀጥታ፡

በቡታጅራ ከተማ በ500 ሚሊዮን ብር የፍሳሽ ማጣሪያ ግንባታ ሊከናወን ነው

ቡታጅራ፤ ሚያዝያ 28/2017(ኢዜአ)፦በቡታጅራ ከተማ በ500 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው የፍሳሽ ማጣሪያ ግንባታ ፕሮጀክት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

የመሰረት ድንጋዩን ዛሬ ያስቀመጡት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ናቸው።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ከጣልያን መንግስት በተገኘ ድጋፍ የሚከናወን ሲሆን ግንባታው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆንም ተገልጿል።


 

በመርሃ-ግብሩ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙን (ዶ/ር ኢ/ር) ጨምሮ የክልሉ፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞንና የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ መንገዶች ባለስልጣን በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ በ25 ሚሊዮን ብር የተገነባውን የአሳስ ድልድይ ፕሮጀክትንም ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡

ድልድዩ የምስራቅ ጉራጌ እና የስልጤ ዞኖችን የሚያገናኝ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ የመንገድና የውሃ ፕሮጀክቶች በርዕሰ-መስተዳድሩ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም