ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 28/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

የዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከ30 በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል ይደረጋል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ32 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ላይ ይገኛል። ቅዱስ ጊዮርጊስ በ37 ነጥብ 7ኛ ደረጃን ይዟል።

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ይጫወታሉ።

የአምናው የሊጉ አሸናፊ ንግድ ባንክ በ36 ነጥብ 8ኛ ደረጃን ሲይዝ ወልዋሎ በ12 ነጥብ የመጨረሻው 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ስሑል ሽሬ ከፋሲል ከነማ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ የዕለቱ የመጨረሻ መርሃ ግብር ነው።

ስሑል ሽሬ በ19 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ፋሲል ከነማ በ34 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

በወራጅ ቀጠና የሚገኙት ስሑል ሽሬ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረትን ስቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም