የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳር አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳር አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 27/2017(ኢዜአ)፦የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳር በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ጊዲዮን ሳር ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ እና የእስራኤልን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።