የመጀመሪያው የዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ትብብር ፎረም እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የመጀመሪያው የዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ትብብር ፎረም እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 27/2017(ኢዜአ)፦የመጀመሪያው የዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ትብብር (ሊያንዩንጋንግ) ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣የዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ትብብር ፎረም ሊቀ-መንበር (ሊያንዩንጋንግ) ትሳንግ ዋኢ-ሁንግ፣ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ፖሊስ ኮሚሽን ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ትብብር ፎረም (ሊያንዩንጋንግ) የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆና መመረጧ ይታወቃል።
ፎረሙ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን ጉባኤ እያካሄደም ይገኛል።
በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፤ፎረሙ በመተባበር የጋራ ደህንነትን በማስጠበቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ የሕዝቦችን ደህንነት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደምትገኝም ተናግረዋል።
ትብብሩ ይበልጥ እንዲጠናከርም ኢትዮጵያ የምታበረክተውን አስተዋጸኦ አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።
የዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ትብብር ፎረም ሊቀ-መንበር (ሊያንዩንጋንግ) አንዲ ትሳንግ በበኩላቸው፥ ፎረሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግጭቶችንና ዋና መንስኤዎችን ለማስወገድ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የጋራ ደህንነትን በማስጠበቅ ዙሪያ ያሉ የጋራ ጥረቶችን ለማበረታታት እየሰራ መሆኑንም ጠቁመው፥ የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በጋራ ለመግታት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ፎረሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራም ነው የጠቆሙት።